Information on Amhara Region Diaspora Festival (Planned for 2016)

Note: The Oromia Diaspora Festival takes place in August 2015. The Amhara Diaspora Festival will take place in the summer of 2016.

ለመላው የአማራ ተወላጆች ኢትዮጵያንና ትውልደ-ኢትጵያን በሙሉ የቀረበ የልማት ጥሪ፣

እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ የዳያስፖራ ቀን ከነሐሴ6-10/2007 ዓ.ም ( ከኦገስት 12-16/2015) በአዲስ አበባ በታላቅ ድምቀት ለማክበር ከፍተኛ እንቅስቃሴ በመደረግ ላይ ነው፡፡ ይሕው ብሔራዊ የዲያስፖራ በዓል አከባበር እንደተጠናቀቀ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአማራ ተወላጆች ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ-ኢትጵያዊያንን በክልሉ ባለፋት ሁለት አስርት አመታት ባካሄደችው ዘርፈ ብዙ የልማት እንቅስቃሴዎችንና የተገኙ ውጤቶችን በማስጎብኘት የፓናል ውይይት ለማድረግና በቀጣይ በክልሉ የኢንቨስትመንት ፍሰት የሚጠናክርበትና የዲያስፖራው ተሳትፎና ተጠቃሚነቱን ለማጎልበት በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ለመምከር በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እስካሁን በክልሉ ለተመዘገቡት ውጤቶች መገኘት የክልሉ መንግስትና መላው የክልሉ ህዝብ ትኩረታቸውን ድህነትን በማስወገድ ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጠ ባደረጉት ሁለንተናዊ ርብርብ ላይ የዲያስፖራው ሚና ልዩ ስፍራ ሊሰጠው እንደሚገባው ያምናል፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሁኖ ሀገራችን በ2017 መካከለኛ ገቢ (low middle income) ካላቸው አገሮች ተርታ ለማሰለፍ በሚደረገው ርብርብ ላይ የክልሉ መንግስት የበኩሉን ሚና እንዲያበረክት ማስቻል ሲሆን በቀጣዩ ሁለተኛው የአምስት አመት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን መንግስት፤ የክልሉ ህዝብና ድርጅታችን ብአዴን በተደራጀና በተቀናጀ አግባብ ከግብርና ወደ ኢንደስትሪ በሚደረገው መዋቅራዊ ሽግግር እና የሀገሪቱን ሕዳሴ ለማረጋገጥ በሚደረገው ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ዳያስፖራው እያበረከተ ያለውን ድርሻ ይበልጥ በማጐልበትና በማጠናከር፣በክልሉ/በሀገሪቱ የትራንስፎርሜኑን ጉዞ ስኬታማ ለማድረግ የላቀ ሚና ለመጫወት ነው፡፡

ከላይ የተገለፀውን ክልላዊና ሀገራዊ ግብ ለማሳካት፤ ክልሉን ለማልማትና በየደረጃው የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በዚሁ ዘርፈ ብዙ የልማት እንቅስቃሴ ላይ የአማራ ተወላጆች ኢትዮጵና ትውልደ-ኢትጵያንን በጉዳዩ ላይ በግልፅ በማወያየትና መግባባት ላይ በመድረስ ከወትሮው በተለዬ መልኩ ተሳትፏቸውንና ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ ሰፊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ነው፡፡ በመሆኑም ከላይ በተደጋጋሚ እንደተገለፀው የጉብኝቱና ውይይቱ መሠረታዊ ዓላማ የአማራ ተወላጆች ኢትዮጵያንና ትውልደ-ኢትጵያንን ከክልላቸው ብሎም ከሀገራቸው ጋር ያላቸውን ትስስር ይበልጥ በማጠናከር ራሳቸውን ሕዝባቸውንና ሀገራቸውን እንዲጠቅሙ በሚያስችሏቸው መስኮች ሁሉ የነቃና የተደራጀ ተሳትፎቸውን ለማጎልበት የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎችን በጋራ ምክክር ለማረጋገጥ ያለመ ነው፡፡

ስለሆነም ከተለያዩ የዓለም አገራት በአዲስ አበባ ለሚከበረው ብሔራዊ የዲያስፖራ በዓል አከባበር፣ በራሳችሁ ፕሮግራም ወደ አገር ቤት የመጣችሁ፣ እንዲሁም በተለያዩ የአገራችን አካባቢዎች በኢንቨስትመንትና በልዩ ልዩ ሙያና የልማት ሥራዎች ላይ በመሳተፍ ላይ ያላችሁ የአማራ ተወላጆ ኢትዮጵያንና ትውልደ-ኢትጵያን የብሔራዊ በዓል አከባበሩ እንደተጠናቀቀ በክልሉ ርዕሰ ከተማ ባህር ዳር ላይ በሚደረገው የምክክር መድረግ ላይ እንድትገኙለት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በአክብሮት ጥሪውን እያቀረበ በያላችሁበት ሆናችሁ በኦንላየን መመዝገብ ትችሉ ዘነድ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት ሥራውን የሚያስተባብሩ ባለሙያዎች፡-

1. አቶ ደመቀ ዘመነ ሽፈራው  ሞባይል፡ +251 913 81 37 80  የኢሜል አድራሻ፡ dzemene@aol.com

2. ከበደ በየነ ብሩ  ሞባይል፡ +251 939 48 04 83 የኢሜል አድራሻ፡ kebede2310@yahoo.com

3. ሞላልኝ አስፋው አያና ሞባይል፡ +251 911 22 10 53 የኢሜል አድራሻ፡ amolalign@yahoo.com

እንዲያስተባብሩ የተወከሉ መሆናቸውን እየገለፀ ያገሩን ሠርዶ በሀገሩ …. እንዲሉ፣ መላ የአማራ ተወላጆች ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በህዳሴ ግስጋሴ ላይ ወደምትገኘው ክልላችሁ እንድትመጡና በክልሉ እየተከናወኑ ያሉ ዋና ዋና የልማት ፕሮጀክቶች ጉብኝትና በፓናል ውይይቱ ላይ እንድትሳተፉ በክብር ተጠርታችኋል፡፡ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ባህር ዳር እጅ ለእጅ ተያይዘን የክልላችንንም ሆነ የሀገራችንን ህዳሴ እናረጋግጣለን!!

For a PDF Version, please click here:
Amhara Diaspora

=====

 

 

Advertisements

One Response

  1. Now we have one year to plan for traveling , but for this year was very short notice not even 2 month. I hope it will continue posting a head of time

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: